ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ 150 ሺ ዶላር ተሸለሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ የዩኔስኮ የ2019 የሠላም ተሸላሚ ሆኑ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰላምን ለማምጣት፣ ለማስጠበቅና ለማቆየት ላደረጉት አስተዋፅኦ የዩኔስኮ ፌሊኒክስ ሃፌፍ- ቦኒይ የሰላም ሽልማት 2019 አሸናፊ ሆኑ።

የዩኔስኮ ፌሊኒክስ ሃፌፍ- ቦኒይ የሰላም ሽልማት ለሃያ በላይ አለም አቀፍ ታዋቂ ግለሰቦች እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1991 ጀምሮ ሲሰጥ ቆይቷል።

ይህ ሽልማት “ዓለም አቀፍ ግጭቶችን በመፍታት፣ የውይይትን እና ድርድርን ሚና በማጉላትና በመቻቻል፣ በእኩልነትና በመግባባት ሰላም እንዲሰፍን አስተዋፅኦ ላደረጉ ግለሰቦች” ይሰጣል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ሽልማት ያገኙት በኢትዮጵያ ሠላምን ለማምጣት፣ ለማስጠበቅና ለማቆየት እንዲሁም የፕረስ ነፃነት እንዲሰፍን ላደረጉት አስተዋፅኦ መሆኑ ተገልጿል። ዩኔስኮ  የሠላም ተሸላሚ በየዓመቱ 150 ሺ ዶላር/ወደ 5 ሚሊየን ብር / የሚ    ሸለም  ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገንዘቡን ለሸገር ማስዋቢያ ፕሮጀክት ያውሉታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

UNESCO awarded Prime Minister Abiy Ahmed the Félix Houphouët-Boigny Prize for Peace for his commendable work in pursuit of peace. The Félix Houphouët-Boigny Prize for Peace has awarded more than 20 world figures since 1991.

The awards go to individuals who have “actively contributed to bring peace by solving international conflicts, by searching dialogue and negotiation in their conciliation role and by achieving ecumenical understanding for tolerance.”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe